ለኢትዮጵያ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች የ2010 ዓ.ም መግቢያ ፈተና የምዝገባ ጥሪ
በአገራችን እየተመዘገበ ያለውን የኢኮኖሚ እድገት ለማስቀጠልና የአገሪቱን በሳይንስና ቴክኖሎጂ የሰለጠነ የሰው ሀይል ፍላጎት ለማሟላት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ከፍተኛ የለውጥ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ይህንንም እውን ለማድረግ ልዩ ተልዕኮ ተሰጥቷቸው በስሩ የተደራጁትን የአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራት ማዕከላት በማድረግ በዘርፉ ብቃት ያላቸውን ሙያተኞችን እያፈራ ይገኛል፡፡
በመሆኑም በ2010 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ እና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በአፕላይድ ሳይንስና በኢንጂነሪንግ ዘርፎች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ በ 2009 ዓ.ም. የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የወሰዱና ከታች የተጠቀሱትን ዝርዝር መስፈርቶች የሚያሟሉ ተማሪዎችን ተጨማሪ የመግቢያ ፈተና በቀጥታ (online) በመስጠት መቀበል ይፈልጋል፡፡
የመመዝገቢያ መስፈርቶች:-

 • በኢንጂነሪንግ ትምህርት መስክ መሰልጠን ለሚፈልጉ:- ለታዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ), ለወንዶች ከ410 በላይ፣ ለሴቶች ከ400 በላይ የሆነ, ለሌሎች ክልሎች:-
  ለወንዶች ከ425 በላይ፣ ለሴቶች ከ410 በላይ የሆነ
 • በአፕላይድ ሳይንስ ትምህርት መስክ መሰልጠን ለሚፈልጉ:-- ለታዳጊ ክልሎች:-ለወንዶች ከ350 በላይ፣ ለሴቶች ከ335 በላይ የሆነ- ለሌሎች ክልሎች:-ለወንዶች ከ375 በላይ፣ ለሴቶች ከ350 በላይ የሆነ
  የትምህርት መስኮች:-
  አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ   አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ
 ኢንጂነሪንግ  አፕላይድ ሳይንስ  ኢንጂነሪንግ  አፕላይድ ሳይንስ
አርክቴክቸር ባዮቴክኖሎጂ አርክቴክቸር አፕላይድ ባዮሎጂ
ሲቪል ኢንጂነሪንግ ኢንዱስትሪያል ኬሚስትሪ ሲቪል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ኬሚስትሪ
ኬሚካል ኢንጂነሪንግ ፉድ ሳይንስና አፕላይድ ኒዩትሪሽን ኬሚካል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ፊዚክስ
ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ ጅኦሎጂ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ጅኦሎጂ
ኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጂነሪንግ ኤሌክትሮኒክስ ፓወር እና ኮንትሮል ኢንጂነሪንግ አፕላይድ ማቲማቲክስ        
ኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪንግ   ኤሌክትሮኒክስ እና ኮሚኒኬሽን ኢንጂነሪንግ     
ሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ   ኮምፒዩተር ሳይንስና ኢንጂነሪንግ  
ኢንቫይሮሜንታል ኢንጂነሪንግ      ወተር ሪሶርስ ኢንጂነሪንግ  
ማይኒንግ ኢንጂነሪንግ   ማቴሪያል ሳይንስና ኢንጂነሪንግ  

የምዝገባ ጊዜ:- ከነሐሴ 15 እስከ 21 ቀን 2009 ዓ.ም. ምዝገባው የሚጠናቀቀው:- ነሐሴ 21 ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ይሆናል::
የምዝገባ ቦታ:- የምዝገባ መስፈርቱን የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ cba.astu.edu.et ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ::
ፈተናው የሚሰጥበት ቀን:- ጳጉሜ 1 ቀን 2009 ዓ.ም.  ከጧቱ 2:00 ሰዓት እስከ ቀኑ 11:30 ሰዓት
ፈተናው የሚሰጥበት ቦታ:- በምዝገባ ወቅት በመረጡት የፈተና ጣቢያ በአካል በመቅረብ ይሆናል::

ማሳሰቢያ:-
1)    ለምዝገባና ለፈተና ምንም አይነት ክፍያ አይጠየቅም፣
2)    ከሚመዘገቡት አመልካቾች ውስጥ ለፈተና የሚቀርቡት ስም ዝርዝራቸው በድህረ-ገፅ:-
www.most.gov.et    www.aastu.edu.et      www.astu.edu.et
እንደአመቺነቱም በስልክ አጭር የጽሑፍ መልዕክት የሚገለፅ ይሆናል::
3)    አመልካቾች ከወዲሁ ፈተናው በሚሰጥባቸው የትምህርት ዓይነቶች፣ ማለትም የመሰናዶ (11ኛ እና 12ኛ ክፍል) ባዮሎጂ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ሂሳብና እንግሊዝኛ እንዲዘጋጁ ይመከራል::
4)    ፈተና የሚሰጠው በቀጥታ (online) ስለሆነ አመልካቾች በፈተና ጊዜ ሊያጋጥም የሚችል ግራ መጋባትን ለማስቀረት በምዝገባ ጊዜ ከመመዝገቢያ ፎርማቱ ጋር ተያይዞ የቀረበውን የሙከራ ፈተና እንዲለማመዱ ይመከራል::
5)    አመልካቾች ለፈተና ሲቀርቡ የ2009 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ውጤት፣ የሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና አድሚሽን ካርድ (ወይም መታወቂያ) እና የምዝገባ ማረጋገጫ ኮፒ መያዝ ይጠበቅባቸዋል::
6)    የመግቢያ ፈተናውን የሚያልፉ አመልካቾች በትምህርት ሚኒስቴር በኩል የሚደረገው የዩኒቨርሲቲ ምደባ ውስጥ አይካተቱም::
7)    በውጤታቸው የተመረጡ ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከላይ በተጠቀሱት ድህረ-ገፆች ይገለፃል::
8)    በመስፈርቱ መሰረት ያልተመረጡ አመልካቾች ከዚህ በፊት እንደሚደረገው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች የሚመደቡ ይሆናል::
9)    በፈተናው ዕለት ማንኛውንም የሞባይል ስልኮችን ይዞ ወደ መፈተኛ ጣቢያ መግባት የተከለከለ ነው::
10)    በፈተና ወቅት ያልተገባ ተግባር መፈፀም በጥብቅ የተከለከለ ነው::

ለተጨማሪ ማብራሪያ ከላይ የተጠቀሱትን ድህረ ገፆች መጎብኘት ይቻላል::               የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የሳይንስና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር

 

Calendar

July 2024
MTWTFSS
1234567
891011121314
15161718192021
22232425262728
293031

Upcoming Events

 

 

Students Services
Connect with us

We're on Social Networks.

Follow us & get in touch.
       

Media Gallery

 • 1.jpg
 • 1a.jpg
 • 2.jpg
 • 3.jpg
 • 3a.jpg
 • 3aa.jpg
 • 3b.jpg
 • 4.jpg
 • 5.jpg
 • 6.jpg
 • 7a.jpg
 • 8.jpg
 • 8a.jpg
 • 8aa.jpg
 • 8b.jpg
 • 8c.jpg
 • 8d.jpg
 • 8f.jpg
 • 8g.jpg
 • 8i.jpg
 • 8j.jpg
 • 9.jpg
 • 9a.jpg
 • 9aa.jpg
 • 9b.jpg
 • 9bb.jpg
 • 9c.jpg
 • 9d.jpg
 • 9f.jpg
 • 9g.jpg

ASTU Campuse Map

maps1

Contact us

International Relations and Corporate Communications
Office: +251 -22-211-3961,  Email: irccd@astu.edu.et
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia
Office of Registrar  
Office: +251 -221-100001,  Email: sar@astu.edu.et
P.O.Box: 1888 Adama, Ethiopia


   © 2020  Adama Science and Technology University